Sport

ሊቨርፑልና ቶተንሃም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ቆይታቸው ዛሬ ይወሰናል

ሊቨርፑልና ቶተንሃም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ቆይታቸው ዛሬ ይወሰናል

አርትስ ሰፖርት 02/04/2011

የ2018/19 የአውሮፓ ቻፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ምሽት ይከናወናሉ፡፡

ዛሬ ምሽት ከ2፡55 ጀምሮ ከምድብ አንድ እስከ አራት የሚገኙ ቡድኖች የምድብ ስድተኛ ግጥሚያቸውን ሲያካሂዱ ከምድብ አራት ምሽት 2፡55 ላይ ሻልከ 04 ከ ሎኮሞቲቭ ሞስኮ፣ ጋላታሳራይ ከ ፖርቶ ይጫወታሉ፡፡ ሻልከና ፖርቶ የጥሎ ማለፉን ዙር ተዋህደዋል፡፡

ምሽት 5፡00 ላይ ደግሞ በምድብ አንድ ክለብ ብሩዥ ከ አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ፣ ሞናኮ ከ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ይገናኛሉ፤ አትሌቲኮና ዶርትሙንድ ወደ ቀጣዩ ዙር ተቀላቅለዋል፡፡ በሁለተኛው ምድብ ከሁሉ አስቀድሞ ዙሩን የተሻገረው ባርሴሎና በኑካምፕ ከቶተንሃም ይፋለማል፣ ኢንተር ሚላን ደግሞ ከ ፒ.ኤስ.ቪ አይንዶቨን ግጥሚያቸውን ያከናውናሉ፡፡ ቶተንሃም ወደ ቀጣዮ ዙር ለማለፍ ማሸነፍ አሊያም ተሸንፎ ኢንተርም በፒ.ኤስ.ቪ መረታት ይኖርበታል፤ አሊያም ሁለታቸውም ጨዋቸውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡

በምድብ ሶስት እስካሁን ያለፈ ቡድን የሌለ ሲሆን የእንግሊዙ ግን ከሁሉም ሊቨርፑል አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፤ በምሽቱ በአንፊልድ ናፖሊን ያስተናግዳል፡፡ ቀያዮቹ ወደ ጥሎ ማለፉ ለመቀላቀል 1 ለ 0 ማሸነፍ አሊያ በሁለት ግብ ልዩነት ድል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ ፒ.ኤስ.ጂ ወደ ሰርቢያ አቅንቶ ሬድ ስታር ቤልግሬድን ይገጥማል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button