EconomyEducationEthiopiaSocial

የራስ መኮንን አዳራሽን ለማደስ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ስምምነት ተፈረመ

አርትስ 02/04/2011

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ የሚገኘውን የራስ መኮንን አዳራሽ ለማደስ ከሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በላይ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ በጃፓን ኤምባሲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት መካከል ነው የተፈረመው።

ስምምነቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኩል የኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ ሀሰን፣ በጃፓን በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳሱኪ ማትሲንጋ ናቸው የፈረሙት።

በስምምነቱ መሰረት አዳራሹ ከመታደሱም በላይ በአዳዲስ መሳሪያዎች የሚደራጅ ይሆናልም ነው የተባለው።

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያና ጃፓን ለዘመናት የዘለቀ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button