EthiopiaSocial

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ‘ኢንዴንጀር ሄልዝ’ ተቋም ን አነጋገሩ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ‘ኢንዴንጀር ሄልዝ’ ተቋም ን አነጋገሩ

አርትስ 3/04/11

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  በጤናማ ስነጾታና ስነተዋልዶ ዙሪያ የሚሰራውን  ኢንዴንጀር ሄልዝተቋም ፕሬዚዳንት  በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡

የተቋሙ ፕሬዚዳንት ትሬሲ ኤል ቤይርድን ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ድርጅቱ በአማራ ክልል ውስጥ ሞዴል የቤተሰብ ምጣኔ ላይ ያተኮረ ስራ በማከናወን የሚያበረታታ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ  ሴቶች በጾታ ልዩነት ሳይገደቡ መብታቸውን እንዲያስከብሩና በሚመለከታቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዲችሉ ድርጅታችን  አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ በበኩላቸው ወጣት ሴቶች በተለይ በትምህርት ወቅት በሁለንተናዊ መልኩ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ ተቋሙ  ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እንዲያከናውን ፕሬዚዳንቷ  ጥሪያቸውን አቅርበዋል ፡፡ መረጃው የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button