World News

ፒዮንግያንግና ሴኡል ቀጠናውን ከኒውክሌር ስጋት ነፃ ለማድረግ ተነሳሽነታቸው ጨምሯል፡፡

ፒዮንግያንግና ሴኡል ቀጠናውን ከኒውክሌር ስጋት ነፃ ለማድረግ ተነሳሽነታቸው ጨምሯል፡፡

አርትስ 21/04/2011

 የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ሙን ጃይ ኢን ጋር  በአዲሱ ዓመት ለመገናኘት ፍላጎት አለኝ ብለዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ኪም ወደ ሴኡል በፃፉት ደብዳቤ ሁለቱ ሀገሮች በመካከላቸው የነበረውን የጥላቻ መንፈስ ለማስወገድ  ያከናወኑትን ታሪካዊ ተግባር አድንቀዋል፡፡

በኮሪያ ልሳነ ምድር አስተማማኝ ሰላም የማስፈን ዓላማቸውን ለማሳካት የሁለቱ መሪዎች መልካም ግንኙነት ወሳኝ መሆኑንም ኪም ተናግረዋል፡፡

ኪም በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ ሴኡል ተጉዘው ከሙን ጃይ ኢን ጋር ለመወያየት ይዘውት የነበረው እቅድ ሳይሳካ በመቅረቱ ሀዘን እንደተሰማቸውም በላኩት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ መንግስት ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው ኪም በአዲሱ ዓመት በአካባቢው ፍፁም ሰላም እንዲሰፍን እና  ሁለቱ ሀገራት ለጋራ ብልፅግና ተባብረው ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡

የሁለቱ ኮሪያዎች መሪዎች ባለፈው ዓመት ሶስት ጊዜ ያህል ተገናኝተው ያደረጓቸው ውይይቶች ውጤታማ እንደነበሩ ሁለቱም ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡

ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ግንኙነታቸው ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያግዛቸውን የባቡር ትራንስፖርት ፕሮጀክት በጋራ ለመገንባት ያደረጉት ስምምነት በመካከላቸው ያለውን መልካም ግንኙነት ያሳያል ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button