EthiopiaSport

ሊቨርፑል የቻምፒዮንስ ሊግ ቆይታው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

አርትስ ስፖርት 20/03/2011

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፤ ከምድብ አንድ እስከ አራት በሚገኙ ቡድኖች መካከልበተደረጉ ጨዋታዎች ወደ ጥሎ ማለፉ የሚገቡ ቡድኖች እየተለዩ ነው፡፡

በምሸቱ በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው ጨዋታ ፓርክ ደፕረንስ ላይ ፒ.ኤስ.ጂ የእንግሊዙን ሊቨርፑል 2 ለ 1 ረትቷል፡፡ ቤርናትናኔይማር ለፓሪሱ ቡድን ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ያስገኙ ግቦችን ከመረብ ሲያዋህዱ፤ ጀምስ ሚልነር የቀያዮቹን ማስተዛዘኛ ግብበፍፁም ቅጣት አስቆጥሯል፡፡ ሊቨርፑል ሽንፈቱን ተከትሎ ወደ ተከታዩ ዙር ተሳታፊ ለመሆን፤ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ናፖሊንከሁለት ግብ በዘለለ ማሸነፍ ይጠበቅበታል፤

በሌሎች ጨዋታዎች ቶተንሃም በዊምብሊ ኢንተር ሚላንን በኢሪክሰን ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፎ፤ የጥሎ ማለፍ ተስፋውለምልሟል፡፡ ከምድቡ ባርሴሎና በሜሲና ፒኬ ጎሎች ፒ.ኤስ.ቪ አይንዶቨንን 2 ለ 1 ረትቷል፡፡

በምሽቱ ናፖሊ ሬድ ስታር ቤልግሬድን፣ ፖርቶ ሸልከን በተመሳሳይ 3 ለ 1፤ እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ሞናኮን፣ ሎኮሞቲቭሞስኮው ጋላታሳራይን በተመሳሳይ የ2 ለ 0 ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ደግሞ ከ ክለብ ብሩዥ ጋር ያለግብ አቻተለያይቷል፡፡

አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ቦርሲያ ዶርትሙንድ፣ ባሴሎና፣ ፖርቶ፣ ሻልከ 04፣ ባየርን ሙኒክ፣ አያክስ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ሮማ፣ዩቬንቱስና ማንችስተር ዩናይትድ ጥሎ ማለፉን የተዋሀዱ ቡድኖች ናቸው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button