EthiopiaPoliticsSocial

የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ በቅርቡ ፀድቆ ወደ ስራ ይገባል ተባለ

ይህህን ያለዉ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሀግ በሪፖርቱ ነዉ፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታዉቋል።

መስሪያ ቤቱ የ2011 በጀት ዓመት የአምሰት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ በርሃኑ ፀጋዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉትም፥ ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በመፅደቅ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ የመደራጀት መበትን የተመለከቱ ዓለም አቀፋዊ እና ህገ መንግስታዊ መርህዎችን ባገናዘበ መልኩ መዘጋጀቱን ዋና አቃቤ ህጉ ተናግረዋል።

የፀረ ሽብር አዋጅንም ለማሻሻል ረቂቅ አዋጅ ዝግጅት የተጠናቀቀ በመሆኑም በቅርቡ ለሚመለከተው አካል ይቀርባል ነው ያሉት።

በተጨማሪም የስነ ስርዓትና ማስረጃ አዋጅ፣ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር አዋጅ፣ የንግድ ህግ፣ የጦር መሳሪያ አያያዝና አስተዳደር አዋጅ፣ የምርጫ ህግ፣ የመረጃ ነፃነትና የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እና የሀይል አጠቃቀም አዋጅን ለማሻሻል የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆች በውይይትመድረኮች ዳብረው እንደሚቀርቡ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

ከፋና እንዳገኘነዉ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ከፍትህ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅት አለመኖር፣ ከፖሊስ ጋር ቅንጅታዊ አሰራር አለመዳበር እና የሰው ሀይል ብቃትና የስነ ምግባር መጓደል ባለፉት አምስት ወራት ያጋጠሙ ችግሮች እንደነበሩ በሪፖርታቸው አንስተዋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button