Africa

የኮንጎ የምርጫ ውጤት ሊዘገይ ይችላል ተባለ

የኮንጎ የምርጫ ውጤት ሊዘገይ ይችላል ተባለ

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ከ59 ዓመት በኋላ  ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይደረግበታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመጀመሪያው ምርጫ ውጤቱ የሚገለፅበት ቀን ሊራዘም እንደሚችል ተነግሯል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን እስካሁን የምርጫው የድመፅ ቆጠራ ውጤት 17 በመቶ ብቻ ነው የደረሰው፡፡

የኮሚሽኑ ፕዝረዳንት ኮርኔል ናንጋ በተቻለን አቅም የምርጫው ጠቅላላ ውጤት በፍጥነት እንዲደርስን ለማድረግ እንሞክራለን ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንቱ የምርጫ ውጤቱን ለህዝ ለማሳወቅ  ምን ችግር እንደገጠማቸው በዝርዝር የተናገሩት ነገር የለም፡፡

በምርጫው በተቃዋሚ ጎራ ለፍክክር የቀረቡት ፌሊክስ ሺሲኬዲ በቃል አቀባያቸው በኩል እንዳሉት የምርጫው ውጤት መዘግየት ሳይሆን የሚያሳስበን ታአማኒነቱ ነው ብለዋል፡፡

ከደቡባዊ አፍሪካ ልማት በማህበረሰብ የተወከሉ የምርጫ ታዛቢዎች በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ላይ በአንፃራዊነት ሰላማዊ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ውጤቱም ልክ እንደ ድምፅ አሰጣጡ ሂደት ሰላማዊ እንደሆን ተስፋውን የገለፀው የታዛቢ ቡድኑ አሁን በዚህ መልኩ ምርጫ መካሄዱ በራሱ ትልቅ ድል ነው ብሏል፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በኢቦላ መከሰት እና በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኮንጓዊያን በምርጫ አልተሳተፉም፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button