EthiopiaSocial

የተማሪዎች የስነ ምግባርና ስነ ዜጋ ገዢ መመሪያ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተማሪዎች የስነ ምግባርና ስነ ዜጋ ገዢ መመሪያ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ይህን ያለው የሚኒስቴሩን የ100 ቀናት የስራ አፈፃፀም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የፖሊሲና እቅድ አፈፃፀም ክትትል ኃላፊዎች ባቀረበበት ጊዜ ነው፡፡

የአፈፃፀም ክትትል ኃላፊዎች በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ እየተመሩ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን በቴክኖሎጂ የዘመነ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን፤  ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴ እና የተጀመረውን የህፃናት ማቆያ እና ጅምናዚየሙን ኃላፊዎቹ ተመልክተው አድንቀዋል ተብሏል፡፡

በመማር ማስተማሩ ሂደት የትምህርት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሃዊነት ላይ የተሰሩ ስራዎችን በትምህርት ሚኒስትሩ እና በማኔጅመንት አባላቱ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከገምጋሚዎቹ በተነሱ ጥያቄዎች የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ ልዩ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ከክልሎች ጋር ወደስራ የተገባ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀው፤ ለዚህም ማስፈፀሚያ 65 ሚሊዮን ብር ለ1400 ትምህርት ቤቶች ተመድቦ ወደ ስራ እንደተገባ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የተማሪዎችን የስነ ምግባርና ስነ ዜጋ ገዢ መመሪያ በማጠናቀቅ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አርትስ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስቡክ ገፅ ባገኘው መረጃ የትምህርት ምዘና እና ፈተና አዘገጃጀትና ስታንዳርድን፤ በመምህራን ብቃት ላይ እና በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ላይ  በትግበራው ወቅት ሊያጋጥሙ በሚችሉ  ጉዳዮች ላይ ውይይትም መካሂዱ በውይይቱ ተብራርቷል፡፡

ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አሁን እየተተገበረ ያለው የመምህራን አሰለጣጠን ከምልመላው ጀምሮ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንና በአራት ዩኒቨርሲቲዎች መሰልጠን መጀመራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ለመጡት የልዑካን ቡድን አባላት ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button