Ethiopia

ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ጎብኝተዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን ሲሉ አስታውቀዋል። ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉም አክለዋል። በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ሲሞቱ፥ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ
አርብቶ አደሮች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button