Social

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ፡፡

ሀበሻ ለፍቅር የሚል ማህበር ያቋቋሙት የኮሚኒቲ አባላቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያ  ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና በዳያስፖራው ተሳትፎ፣ እንዲሁም ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኞች መሆናቸውን የገለጹት የኮሚኒቲ አባላቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ሊተገበር እንደሚገባም በውይይታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

“ለያዝናቸው የለውጥ መንገዶች ትልቁ ደጋፊያችንና አጋራችን በውጪ የሚኖረው ማህበረሰብ ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የለውጡ ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button