Politics

ኢትዮጵያ በሚቀጥለው አመት የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤን እንድታስተናግድ ስምምነት ላይ ተደረሰ

ኢትዮጵያ ሚቀጥለው አመት የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤን እንድታስተናግድ ስምምነት ላይ ተደረሰ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ክላውስ ሻዋብ ጋር በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ 2020 የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤን እንድታስተናግድ ተስማምተዋል።

እንደጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ እና ፕሮፌሰር ሻውብ ቁልፍ የሆኑ ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመፍታት በንግድ፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ እንዲሁም በሲቪል ማህበረሰብ ውስጥ የተቀናጀ አሠራር አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል ።

በተያያዘ ዜናም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዓለም ባንክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ጆርጂዬቫ ክሪስታሊና ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ አድንቀዋል።ባንኩ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button