SportSports

የዝውውር ወሬዎች……

የዝውውር ወሬዎች……

የጥር ወር የባህር ማዶ ተጫዋቾች የዝውውር  መስኮት ሊጠናቀቅ ከሶስት ቀናት ባነሰ ጊዜ እየቀረው ክለቦች ከመሸ በሰፊው ወደ ገበያ ወጥተዋል፡፡

በዛሬ ዕለት የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተቀባበሏቸውን የዝውውር መረጃዎች እንመለከታለን፡፡

በተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ጉዳት እየታመሰ የሚገኘው የእንሊዙ አርሰናል የቼልሲውን ጋሪ ካሂል የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ሚረረ አስነብቧል፡፡

…………………………

እንደ ካልሽዮ መርካቶ ዘገባ ደግሞ ሊቨርፑል የብሬሽያውን አማካይ ሳንድሮ ቶናሊ የማስፈርም ፍላጎት አለው ተብሏል፤ ተጫዋቹን የጣሊያኑ ኤስ ሚላን እንዲሁ ለማስፈርም እየተመለከተው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የ18 ዓመቱ ተጫዋች አዲሱ አንድሪያ ፔርሎ እየተባለ ሲሆን በቀጣይ ዓመታት በአውሮፓ እግር ኳስ እንደሚነግስ አየተተነበየ ይገኛል፡፡

…………………………..

ሰሜን ለንደናውያኑ ቶተንሃሞች ሌስተር ሲቲዎች ወደ ኪንግ ፓወር ለማምጣት አይናቸውን ያሳረፉበትን የሞናኮውን የአማካይ ስፍራ ተጫሰዋች ዮሪ ቴሊማንስ ጣልቃ ገብተው ለመውሰድ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡

ቀበሮዎቹ የ21 ዓመቱን ቤልጅየማዊ ተጫዋች በውሰት ውል አሊያ በግዥ የማስፈረም ውጥን እንዳላቸው ተጠቁሟል፡

…………………………….

የጥር ወር የዝውውር መስኮት ያላሳሳባው አንዳንድ ክለቦችም ለክረምቱ ከአሁኑ እየተዘጋጁ ነው፡፡

ቼልሲዎች የባርሴሎናውን ክሮሽያዊ አማካይ ኢቫን ራኪቲች  ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት እየጣሩ እንደሆነ ደይሊ ኤክስፕረስ መረጃውን እንካችሁ ብሏል፡፡

…………………………….

ማ/ሲዎቲዎች ደግሞ እንግዛዊውን የሌስተር ወጣት ተጫዋች ቤን ችልዌል  በክረምቱ የማዛወር ፍላጎት እናዳለቸው ኢ.ኤስ.ፒ.ኤን ጠቁሟል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button