crimeEthiopiaNewsSocialኢትዮጵያ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች::
የአማራ ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ግለሰቧ በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ ወላጅ 600 ሺህ ብር ከከፈሉ ልጃቸውን ልትመልስ እንደምትችል በስልክ ደውላ ታሳውቃለች። የወረዳው የፀጥታ አካል ህፃኑን ይዛ የሄደችበትን አካባቢ ፈጥኖ በማጣራት ባደረገው ጥብቅ ክትትልና አሰሳ ትናንት በወገራ ወረዳ ግራርጌ በተባለው የገጠር ቀበሌ መያዝ መቻሉን አስታውቀዋል። ህፃንዋም ወላጆቿ እንዲረከቡ መደረጉንና በመልካም ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።በድርጊቱ በዋናና በተባባሪነት የተሳተፉት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ ሂዳት ላይ እንደሚገኝና በድርጊቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሌሎች ሶስት ግለሰቦችም ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል። በቅርቡም በዞኑ በሰው ማገት ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገጽ አስታዉቋል፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button