COVID-19EthiopiaNews

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ዉ 5 ሺ 6 መቶ 36 የላብራቶሪ ምርመራ አንድመቶ ሰባስድስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አስታዉቀዋል፡፡በአጠቃላይም በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 5 መቶ 21 ደርሷል፡፡ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች 116 ወንድ እና 60 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸዉም ከ 5 አስከ 90 ዓመት ዉስጥ ይገኛሉ፡፡በዜግነት 175 ሰዎች ኢትዮጵዉያን ሲሆኑ አንድ ሰዉ የዉጭ ሀገር ዜጋ ነዉ፡፡ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ 98 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፤33 ሰዎች ከአማራ ክልለ ፤31 ሰዎች ከትግራይ ክልል ፤7 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፤3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፤2 ሰዎች ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እና 2 ሰዎች ከአፋር ክልል ናቸዉ፡፡ባለፉት 24 ሰዓታት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ተገልጿል፡፡ አንዱ ከአስክሬን ምርመራ ቫረሱ እንዳለበት የታወቀ ሲሆን፤ ሁለቱ ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ የነበሩ መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡ባጠቃለይ በሀገራችን በቫይረሱ ህይወታቸዉ ያለፉ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል፡፡በሌላበኩል በትላንትናዉ ዕለት 75 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በሀገራችንም ከበሽታዉ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 መቶ 45 ደርሷል::

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button