Africa

ዙማ ከፖሊስ ጋር ድብብቆሽ በቃኝ አሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮቭ ዙማ ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተሰማ፡፡

የተመሰረተባቸውን የሙስና ክስ ችሎት ቀርበው እንዲያስረዱ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ባለማክበር የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው ዙማ ቅጣቱ እንዲቀርላቸው አቤት ብለው ነበር፡፡

የተወሰነባቸውን ቅጣት እንዲፈፅሙ ሲጠየቁ አሻፈረኝ ብለው የነበሩት ፕሬዚዳንቱ ፖሊስ በሃይል ይዞ ወደ አስር ቤት ሊወስዳቸው በሚዘጋጅበት በገዛ ፈቃዳቸው እጃቸውን መስጠታቸው ነው የተሰማው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው በደቡብ አፍሪካ ታሪክ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ተከሰው ሲፈረድባቸውና ሲታሰሩ ታይቶ ስለማያውቅ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ግርምትን ፈጥሯል፡፡

ልጃቸው ዱዱ ዙማ ሳምቡድላ በትዊተር ገጿ ባሰፈረችው ፅሁፍ አባቴ ወደ እስር ቤት እያመራ ነው ግን ትልቅ የመንፈስ ጥንካሬ ይታይበታል ብላለች፡፡

ዙማ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቢመሰረትባቸውም እሳቸው ግን በተደጋጋሚ ንፅህናቸውን በመግለፅ የፖለቲካ ውሳኔ ሰለባ መሆናቸውን ሲናገሩ ይደመጡ ነበር፡፡

ፕሬዚዳንቱ ገና ስልጣናቸውን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ ባለሃብቶች ከፖለቲከኞች ጋር በመመሳጠር እዲከሰሱ ሴራ ይሸረቡባቸው እንደነበረም ወስጥ ውስጡን ይነገራል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button