EthiopiaPolitics

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ  ከአምስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ።

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ  ከአምስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ።
የዛሬ ሰላሳ አመት ገደማ ኢትዮጵያን በመወከል አምባሳደር ሆነው ባገለገሉባት ዳካር ሴኔጋል የሚገኙት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከኢኳቶሪያል ጊኒ አልፋ ኮንዴ ፣ከኮትዲቯሩ አላሳን ኦታራ ፣ከጋምቢያው አዳማ ባሮው ፣ከላይቤሪያ ጆርጅ ዊሃ እና ከቡርኪናፋሶው ክርስቲያን ካቦሬ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል ።
በውይይቱም ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት አላት ፣ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ከሆኑት የአፍሪካ ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነትም በዚሁ ማዕቀፍ የሚታይና ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በየሃገራቱ መካከል የሚቋቋመው የጋራ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ከተለመደው ሁኔታና አሰራር በተለየ ሁኔታ እንዲሁም የሀገራቱን የጋራ ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ በማከናወን ውጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
መሪዎችም በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ግንኙነታቸውን ማሳደግ እንደሚፈልጉ ነው የገለጹት።

መሪዎቹም  የአፍሪካውያን ጥቅሞች እንዲረጋገጡም ኢትዮጵያ የምታደርጋቸውን ጥረቶች አድንቀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button