AfricaPolitics

የደቡብ ሱዳን መሪዎች ስለ ሰላም ሊፀልዩ ወደ ቫቲካን ይጓዛሉ፡፡

የደቡብ ሱዳን መሪዎች ስለ ሰላም ሊፀልዩ ወደ ቫቲካን ይጓዛሉ፡፡

ተቀናቃኞቹ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ዶክተር ሪክ ማቻር   ወደ ቫቲካን ተጉዘው ጡረታ በወጡት ፖፕ ቤነዲክት 16ኛ እጂ ለመባረክ ያሰቡት በሀገራቸው የተጀመረው እርቀ ሰላም ፍፃሜው ያማረ ይሆን ዘንድ በመሻት ነው ተብሏል፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የቫቲካን ቃል አቀባይ አሌሳንድሮ ሶቲን ጠቅሶ እንደፃፈው ሁለቱ መሪዎች በፈረንጆቹ ሚያዚያ 9 እና 10 በቫቲካን ተገኝተው መንፈሳዊ ቡራኬ ያገኛሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀናቃኛቸው  ሪክ ማቻር በመካከላቸው ያለውን ቁርሾ አስወግደው አብረው እንዲሰሩ ሀገራት በጋራ እና በተናጠል ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

አሁን ደግሞ ነገሩን በመንፈሳዊ ጎኑ ተመልክተው በጋራ በሀገራቸው የማይናወጥ ሰላም ይመጣ ዘንድ በፀሎት ለመትጋት ቫቲካን ላይ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ በተደጋጋሚ የደቡብ ሱዳን የሰላም እጦት እንደሚያሳስባቸው ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button