Ethiopia

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በጦር ግንባር ጀብድ ፈፅመው ድል ላመጡ ሴቶች ምስጋና አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ተከብሯል። ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በናንተ ድርብ መስዋዕትነት ሀገር ትቀጥላለችና ለናንተ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የሀገራችን ሰላም በሴቶች ተጋድሎ ይረጋገጣል፤ በጀግና ሴቶች ሰማዕትነት ሀገራችን ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለችም ብለዋል፡፡


አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው ጦርነት ላይ ትልቅ ሚና የነበራቸውና ታሪክ የፃፉ የሴት መከላከያ ሰራዊት አባላት የምስጋና እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በብዙ ችግር ውስጥ ሆነው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ግንባር መዝመታቸው ለእኛ ትልቅ ክብር ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በጦርነቱ ያጣናቸውን ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ሁሌም እናወሳቸዋለን ብለዋል፡፡ ቀኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ “እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ!!” በመከላከያ ደግሞ “የሀገራችን ሰላም በሴቷ ተጋድሎ ህያውነት ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button