Ethiopia

ምርጫው ከነችግሮቹም ቢሆን የተሻለ ሂደት ታይቶበታል-ኢሰመጉ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ መሠረት የጣለና በአንፃራዊነት ስኬታማ እንደነበረ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ። ኢሰመጉ በቅድመ ምርጫ፣ በድምፅ መስጫ ዕለትና ድህረ ምርጫ ወቅቶች ያለውን አጠቃላይ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ምርጫው በተከናወነባቸው በአብዛኞቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጎላ የጸጥታ ችግር አለማጋጠሙን የገለጸው ተቋሙ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሚፈጠሩ ችግሮች ምላሽ የሰጠበትን በጥሩ ጎኑ አንስቷል፡፡ እንዲሁም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ታዛቢዎች ነፃ ሆነው እንዲታዘቡ መደረጉ በምርጫው የታዩ መልካም አጋጣሚዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች አለመዘጋጀቱ፣ በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ
የሚደረገው የምርጫ ገለፃና ማብራሪያ ወጥነት ያልነበረው መሆኑ ደግሞ እንደችግር የሚታይ ነበር ብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ባጋጠመባቸው አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ያለ ምርጫ ቦርድ እውቅና የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች እንዲዘጉ መደረጉ ለሌላው በምርጫው ወቅት ከነበሩ ችግሮች መካከል ይገኙበታል ብሏል። ይህ ቀዳሚ መግለጫ የተዘጋጅው በሁለቱ የድምፅ መስጫ ቀናት በተሰበሰቡ መረጃዎች ብቻ በመሆኑ በቀጣይ ተጨማሪ መረጃዎች ሲገኙ ሊለወጡ የሚችሉ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ
መብቶች ጉባኤ አስታውቋል፡፡ ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button