Social

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከጤና ባለሙያዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይትም የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 26 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን  በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

በጤና ባለሙያዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደመወዝን ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ፥ ውይይቱም በጥያቄዎቹ ላይ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።

የጤና ሚኒስትሩ እንዳስታወቁት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱት የውይይት መድረኮች የመፍትሄ ሃሳቦች ለማስቀመጥ የሚያስችሉ ናቸው  ብለዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button