EthiopiaSocial

ቤተ-እስራኤላውያኑ የፓርኩን ሁኔታ ለማየት ጎንደር ገብተዋል

ቤተ-እስራኤላውያኑ የፓርኩን ሁኔታ ለማየት ጎንደር ገብተዋል

የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ የደረሰበት ክፍል መልሶ ሊያገግም በሚችልበትና ዘላቂ ጥበቃ በሚመቻችበት መንገድ ዙሪያ ጥናት የሚያደርግ የቤተ-እስራኤላውያን ቡድን ዛሬ ረፋድ ጎንደር ገብቷል፡፡

በቀድሞዋ የእስራኤል አምባሳደር በኢትዮጵያ ወይዘሮ በላይነሽ ዛባድያ የሚመራው ልዑክ በቀጣይ ወደ ተቃጠለው የፓርኩ አካባቢ በማቅናት የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለመወሰን የሚያስችል መረጃ በአካል ይሰበስባል፤ ከሰሜን ጎንደር ዞን እና ከአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋርም ይወያያል፡፡

የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በመጋቢትና ሚያዝያ ወራት ባጋጠመው የእሳት ቃጠሎ አደጋ አንድ ሺህ 40 ሄክታር መውደሙ የሚታወስ ነው፡፡

በተለይ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2011ዓ.ም በነበረው ቃጠሎ በፓርኩ ከፍተኛ ውድመት መድረሱና የእስራኤል የእሳት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እና አንድ ሄሊኮፕተር በቦታው መሠማራታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ዘገባው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button