Uncategorized

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ባለፈው ቅዳሜ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ መንግስት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
ሚኒስቴሩ ከጤና ባለሙያዎቹ የተነሱ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ የተመለሱ ጥቄዎች በሚል በዝርዝር ይፋ አደርጓል።
በዚህም መሰረት፦
1. የሀኪሞችና የሌሎች ባለሙያዎች የስራ ምደባ በተመለከተ፦
• አሁን በስራ ላይ ያሉ ሀኪሞችንም ሆነ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች የአለም የጤና
ድርጅት ባስቀመጠው ዝቅተኛ ስታንዳርድ (health work force density) መሰረት በሰራ ለይ ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ህብረተሰቡን ለማገልግል በቂ ስላልሆነ በሚቀጥሉት ኣመታት የሚመረቁ ሀኪሞችም ሆነ ሌሎች ባለሙያዎች መመደብ እንዲቻል ክልሎች በጀትና ተጨማሪ መደብ እንዲያስፈቅዱ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
• ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ በክልሎችና በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ስፖንሰርነት 3ሺህ 800 የስፔሻላይዜሽን ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ሀኪሞች ደሞዝ፣ መደብና ጥቅማጥቅም በጤና ሚኒስቴር እንዲሸፈን በመወሰኑ ተጨማሪ 3ሺህ800 ሀኪሞችን በክልሎችና በዩኒቨርሲቲዎች ለመቅጠር ያስችላል፡፡
2. የስፔሻላይዜሽን ስልጠና በተመለከተ፦
• በግል ፈተና ወስደው መሰልጠን ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የስፔሻላይዜሸን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል፡፡
3. የሀኪሞችን የወጪ መጋራት በተመለከተ፦
• ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ ቀደም የትምህርት ማስረጃ ለማግኘት የሚከፈለው ብር 470ሺህ እንዲቀርና ሃኪሞችም እንደማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በወጪ መጋራት ህግ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
4. ከፌደራል ተቋማት የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ላይ የሚቆረጠውን ታክስ በተመለከተ፦
• በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ሲቆረጥ የነበረው የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ታክስ ከግንቦት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል መንግስት እንዲሸፈን ተወስኗል።
በተመሳሳይ እስከ አሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።
5. የ ባለሞያ ካሪየር ስትራክቸርን በተመለከተ፦
• ከ2009 ዓ.ም ደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ወደ ጎን የነበረውን የካሪየር እድገት ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በተመሳሳይ እስካሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።
6. የጤና ተቋማትን ስታንዳርድ ማሻሻል በተመለከተ፦
• ከዚህ በፊት የተጋነኑ የሚመስሉ የግል ጤና ተቋም ለመክፈት ሲጠየቁ የነበሩ መስፈርቶች እንዲሻሻሉ ተደርጓል፡፤
ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡
7. የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችን የትምህርት እድል በተመለከተ፦
• ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካሪኩለም በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
8. በግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የህክምና ተማሪዎችን በተመለከተ፦
• በግል የህክምና ትምህርት ቤት የሚማሩ የኢንተርን ሀኪሞች ትምህርት ቤቶቹ በሚሰጣቸው የጊዜ ገደብ የተደራጀ ሆስፒታል እስኪኖራቸው በመንግስት ሆስፒታሎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ወርሃዊ ደሞዛቸውንም የሚመደቡበት የመንግስት ጤና ተቋም እንዲከፍላቸው ተወስኗል፡፡
• ከግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የተመረቁና የሚመረቁ ሀኪሞች እንዲሁም ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ባሉት ክፍት መደቦች መቀጠር እንዲችሉ እድሉ ይመቻቻል።
• ከሀምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከግል ህክምና ትምህርት ቤት የተመረቁ ሀኪሞች ከዚህ በፊት 179ሺህ ብር እንዲከፍሉ ወይም ሁለት አመት እንዲያገለግሉ ያስገደድ የነበረው መመሪያ እንዲቀር ተደርጎ የትምህርት ማስረጃቸው እንዲወስዱ ተደርጎአል።
9. የኢንተርን ሀኪሞችን ጥያቄ በሚመለከት፦
• ከላይ በተሰጡት መፍትሄዎች የተመለሱ ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በጤና ባለሞያዎች ለተነሱ ተጨማሪ ጥያቄዎች የጤና ሚኒስቴር በተዋረድ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከዩኒቨረሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመሆን እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡
10. በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎችን በተመለከተ፡
• በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የየጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎች ወጥ እንዲሆኑ በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ መወሰኑ ይታወቃል።
ሁሉም ክልሎች ይሄ መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ ላይ ያልተካተቱ የሙያ ዘርፎች የተጋላጭነት ክፍያን አስመልክቶ በአጭር ጊዜ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡
11. የጤና ፖሊሲን በተመለከተ፦
• ከህብረተሰባችን የጤና ፍላጎት እና የአለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን ለማድረግ ነባሩ የጤና ፖሊሲያችን እንዲከለስ ተወስኖ የተለያዩ የጤና ባለሙያች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸው ይታወቃል፡፡
በተዋረድ በሚደረጉ ተጨማሪ ውይይቶች እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የጤና ባለሙያ ፖሊሲው ላይ አስተያየት መስጠት እንዲችል በመከለስ ላይ የሚገኘው የፖሊሲ ሰነድ የጤና ሚኒስቴር የምረጃ መረብ (ዌብ ሳይት) ላይ ተጭኗል፡፡
12. ለጤናው ሴክተር ትኩረት ሰጥቶ ስለመስራት፦
• መንግስት ለጤናው ሴክተር የሚያሰፈልገውን ትኩረት መስጠቱን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመጥቅስ ያክል የግዢ ስርዓቱን ማሻሻል አንዱና ዋነኛዉ ነው፡፡
እንደማሳያም ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ግዥ ፍጥነትና ጥራት ለማሻሻል ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ
የላቦራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ማለትም ሄማቶሎጂ/ኬሚስትሪ/ጉሉኮሜትርና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ግዢ በፍሬምወርክ ስምምነት ከአውሮፓ እና አሜሪካ ድርጅቶች ጋር ውል ተገብቶ ዘመን አፈራሽ ማሽኖች ከድርጅቶቹ በነጻ እንዲቀርብ እና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ሳይቆራረጡ ከ3 እስከ 5 ዓመታት ማቅረብ እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶዋል፡፡
በዚህ ስምምነት በመጀመሪያ ዙር ከተካተቱ 500 ተቋማት ውስጥ 50 ተቋማት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን÷ 450 ተቋማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በቀጣይ አመት ሁሉንም ጤና ተቋማት እንዲያካትት ይደረጋል፡፡
ለ 2012 ዓ.ም የ 80 አይነት መድሃኒቶችን ግዢ በረጅም ግዜ የ ግዥ ፍሬም ወርክ ስምምነት እንዲፈጸም ተወስኗል።
• ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ብቻ የጤና ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስቴር ያቀረባቸው አምስት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች ተፈቅደዋል፡፡ ከጸድቁት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች መካከል፦
i. ለፌዴራል ሆስፒታሎች የትርፍ ሰዓትና ጥቅማጥቅም ክፍያዎች የሚቆረጠውን የስራ ግብር ለመሸፈን 70 ሚሊዮን ብር በወር
ii. ለ 3ሺህ 800 የስፔሻላይዜሽን ተማሪ ሀኪሞች ደሞዝና ጥቅማጥቅም የሚውል ግማሽ ቢሊዮን ብር፣
iii. ለ50 የማህበረሰብ ፋርማሲ መክፈቻ 50 ሚሊዮን ብር
iv. ለጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ለመድሀኒት እንዲሁም ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ እዳ የሚከፈል ከ ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እና
v. ለመድሀኒት እና ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ የሚውል በእርዳታ ከምናገኘዉ ውጪ ቀድሞ ይመደብ ከነበረው ከ30 ሚሊዮን ዶላር ወደ የ130 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ከመንግስት በጀት በዚህ ዓመት ተፈቅዷል፡፡
• የምግብ፤መድሀኒት፤ጤና ተቋም እና የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን (FMHACA) ተደራራቢ ሀላፊነቶች ወስዶ እየሰራ በመቆየቱ የሚፈለገውን ያክል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ በዚህ አመት በአዋጅ ወደ መድሀኒት እና ምግብ ቁጥጥር (FDA) እንዲቀየር ተደርጓል፡
13. የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በተመለከተ፦
• እነዚህ ሆስፒታሎች በሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ስር ባሉ ዩኒቨርሲቴዎች እንዲሚተዳደሩ ይታወቃል። በእነዚህ ሆስፒታሎች ለይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴርና ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የችግሮቹን መንስኤ እና መፍትሄ አጥንቶ በአጭር ግዚው ውስጥ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
ከእነዚህ በተጨማሪ የተነሱ ጥያቄዎችን እያየ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለውሳኔ የሚያቀርብ ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስቴርና ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች የሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተቋቁሞ በአጭር ግዜ ውሳኔዎችን ያሳውቃል።አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ባለፈው ቅዳሜ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ መንግስት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
ሚኒስቴሩ ከጤና ባለሙያዎቹ የተነሱ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ የተመለሱ ጥቄዎች በሚል በዝርዝር ይፋ አደርጓል።
በዚህም መሰረት፦
1. የሀኪሞችና የሌሎች ባለሙያዎች የስራ ምደባ በተመለከተ፦
• አሁን በስራ ላይ ያሉ ሀኪሞችንም ሆነ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች የአለም የጤና
ድርጅት ባስቀመጠው ዝቅተኛ ስታንዳርድ (health work force density) መሰረት በሰራ ለይ ያሉት ባለሙያዎች ቁጥር ህብረተሰቡን ለማገልግል በቂ ስላልሆነ በሚቀጥሉት ኣመታት የሚመረቁ ሀኪሞችም ሆነ ሌሎች ባለሙያዎች መመደብ እንዲቻል ክልሎች በጀትና ተጨማሪ መደብ እንዲያስፈቅዱ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
• ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ በክልሎችና በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ስፖንሰርነት 3ሺህ 800 የስፔሻላይዜሽን ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ሀኪሞች ደሞዝ፣ መደብና ጥቅማጥቅም በጤና ሚኒስቴር እንዲሸፈን በመወሰኑ ተጨማሪ 3ሺህ800 ሀኪሞችን በክልሎችና በዩኒቨርሲቲዎች ለመቅጠር ያስችላል፡፡
2. የስፔሻላይዜሽን ስልጠና በተመለከተ፦
• በግል ፈተና ወስደው መሰልጠን ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የስፔሻላይዜሸን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል፡፡
3. የሀኪሞችን የወጪ መጋራት በተመለከተ፦
• ከግንቦት ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ ቀደም የትምህርት ማስረጃ ለማግኘት የሚከፈለው ብር 470ሺህ እንዲቀርና ሃኪሞችም እንደማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በወጪ መጋራት ህግ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
4. ከፌደራል ተቋማት የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ላይ የሚቆረጠውን ታክስ በተመለከተ፦
• በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ሲቆረጥ የነበረው የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማጥቅም ክፍያ ታክስ ከግንቦት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል መንግስት እንዲሸፈን ተወስኗል።
በተመሳሳይ እስከ አሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።
5. የ ባለሞያ ካሪየር ስትራክቸርን በተመለከተ፦
• ከ2009 ዓ.ም ደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ወደ ጎን የነበረውን የካሪየር እድገት ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በተመሳሳይ እስካሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ለይ ተደርሷል።
6. የጤና ተቋማትን ስታንዳርድ ማሻሻል በተመለከተ፦
• ከዚህ በፊት የተጋነኑ የሚመስሉ የግል ጤና ተቋም ለመክፈት ሲጠየቁ የነበሩ መስፈርቶች እንዲሻሻሉ ተደርጓል፡፤
ከግንቦት 2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡
7. የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችን የትምህርት እድል በተመለከተ፦
• ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተቀናጀ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካሪኩለም በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
8. በግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የህክምና ተማሪዎችን በተመለከተ፦
• በግል የህክምና ትምህርት ቤት የሚማሩ የኢንተርን ሀኪሞች ትምህርት ቤቶቹ በሚሰጣቸው የጊዜ ገደብ የተደራጀ ሆስፒታል እስኪኖራቸው በመንግስት ሆስፒታሎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ወርሃዊ ደሞዛቸውንም የሚመደቡበት የመንግስት ጤና ተቋም እንዲከፍላቸው ተወስኗል፡፡
• ከግል የህክምና ትምህርት ቤቶች የተመረቁና የሚመረቁ ሀኪሞች እንዲሁም ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ባሉት ክፍት መደቦች መቀጠር እንዲችሉ እድሉ ይመቻቻል።
• ከሀምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከግል ህክምና ትምህርት ቤት የተመረቁ ሀኪሞች ከዚህ በፊት 179ሺህ ብር እንዲከፍሉ ወይም ሁለት አመት እንዲያገለግሉ ያስገደድ የነበረው መመሪያ እንዲቀር ተደርጎ የትምህርት ማስረጃቸው እንዲወስዱ ተደርጎአል።
9. የኢንተርን ሀኪሞችን ጥያቄ በሚመለከት፦
• ከላይ በተሰጡት መፍትሄዎች የተመለሱ ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በጤና ባለሞያዎች ለተነሱ ተጨማሪ ጥያቄዎች የጤና ሚኒስቴር በተዋረድ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከዩኒቨረሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመሆን እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡
10. በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎችን በተመለከተ፡
• በክልሎች እና በፌድራል ተቋማት እየተደረጉ የሚገኙት የተለያዩ የየጤና ባለሞያ ጥቅማጥቅም ክፍያዎች ወጥ እንዲሆኑ በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ መወሰኑ ይታወቃል።
ሁሉም ክልሎች ይሄ መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በ2005ዓ.ም በወጣው የጥቅማጥቅም መመሪያ ላይ ያልተካተቱ የሙያ ዘርፎች የተጋላጭነት ክፍያን አስመልክቶ በአጭር ጊዜ እንዲካተቱ ይደረጋል፡፡
11. የጤና ፖሊሲን በተመለከተ፦
• ከህብረተሰባችን የጤና ፍላጎት እና የአለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን ለማድረግ ነባሩ የጤና ፖሊሲያችን እንዲከለስ ተወስኖ የተለያዩ የጤና ባለሙያች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸው ይታወቃል፡፡
በተዋረድ በሚደረጉ ተጨማሪ ውይይቶች እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የጤና ባለሙያ ፖሊሲው ላይ አስተያየት መስጠት እንዲችል በመከለስ ላይ የሚገኘው የፖሊሲ ሰነድ የጤና ሚኒስቴር የምረጃ መረብ (ዌብ ሳይት) ላይ ተጭኗል፡፡
12. ለጤናው ሴክተር ትኩረት ሰጥቶ ስለመስራት፦
• መንግስት ለጤናው ሴክተር የሚያሰፈልገውን ትኩረት መስጠቱን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመጥቅስ ያክል የግዢ ስርዓቱን ማሻሻል አንዱና ዋነኛዉ ነው፡፡
እንደማሳያም ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ግዥ ፍጥነትና ጥራት ለማሻሻል ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ
የላቦራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ማለትም ሄማቶሎጂ/ኬሚስትሪ/ጉሉኮሜትርና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ግዢ በፍሬምወርክ ስምምነት ከአውሮፓ እና አሜሪካ ድርጅቶች ጋር ውል ተገብቶ ዘመን አፈራሽ ማሽኖች ከድርጅቶቹ በነጻ እንዲቀርብ እና ሪኤጀንቶች/ኬሚካሎች ሳይቆራረጡ ከ3 እስከ 5 ዓመታት ማቅረብ እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶዋል፡፡
በዚህ ስምምነት በመጀመሪያ ዙር ከተካተቱ 500 ተቋማት ውስጥ 50 ተቋማት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን÷ 450 ተቋማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በቀጣይ አመት ሁሉንም ጤና ተቋማት እንዲያካትት ይደረጋል፡፡
ለ 2012 ዓ.ም የ 80 አይነት መድሃኒቶችን ግዢ በረጅም ግዜ የ ግዥ ፍሬም ወርክ ስምምነት እንዲፈጸም ተወስኗል።
• ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ብቻ የጤና ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስቴር ያቀረባቸው አምስት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች ተፈቅደዋል፡፡ ከጸድቁት የበጀት ጭማሪ ጥያቄዎች መካከል፦
i. ለፌዴራል ሆስፒታሎች የትርፍ ሰዓትና ጥቅማጥቅም ክፍያዎች የሚቆረጠውን የስራ ግብር ለመሸፈን 70 ሚሊዮን ብር በወር
ii. ለ 3ሺህ 800 የስፔሻላይዜሽን ተማሪ ሀኪሞች ደሞዝና ጥቅማጥቅም የሚውል ግማሽ ቢሊዮን ብር፣
iii. ለ50 የማህበረሰብ ፋርማሲ መክፈቻ 50 ሚሊዮን ብር
iv. ለጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ለመድሀኒት እንዲሁም ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ እዳ የሚከፈል ከ ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እና
v. ለመድሀኒት እና ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ የሚውል በእርዳታ ከምናገኘዉ ውጪ ቀድሞ ይመደብ ከነበረው ከ30 ሚሊዮን ዶላር ወደ የ130 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ከመንግስት በጀት በዚህ ዓመት ተፈቅዷል፡፡
• የምግብ፤መድሀኒት፤ጤና ተቋም እና የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን (FMHACA) ተደራራቢ ሀላፊነቶች ወስዶ እየሰራ በመቆየቱ የሚፈለገውን ያክል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ በዚህ አመት በአዋጅ ወደ መድሀኒት እና ምግብ ቁጥጥር (FDA) እንዲቀየር ተደርጓል፡፡a
13. የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በተመለከተ፦
• እነዚህ ሆስፒታሎች በሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ስር ባሉ ዩኒቨርሲቴዎች እንዲሚተዳደሩ ይታወቃል። በእነዚህ ሆስፒታሎች ለይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴርና ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የችግሮቹን መንስኤ እና መፍትሄ አጥንቶ በአጭር ግዚው ውስጥ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
ከእነዚህ በተጨማሪ የተነሱ ጥያቄዎችን እያየ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለውሳኔ የሚያቀርብ ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስቴርና ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች የሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተቋቁሞ በአጭር ግዜ ውሳኔዎችን ያሳውቃል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button