EthiopiaPolitics

የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡

የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡

የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በተፅእኖ ፈጣሪ የሀገር  ሽማግሌዎች  መፍትሄ ሰጪነት  መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ ገልጿል፡፡

በመተከል ዞን  ሰሞኑን የተከሰተው  የሰብአዊ ቀውስና የፀጥታ ችግር  የሚፈታው  ከነዋሪዎች  በሚመነጭ  የሰላም ፍላጎት እና በተፅእኖ ፈጣሪ  የሀገር ሽማግሌዎች መሆኑም  ተነግሯል፡፡

የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንደገለፀው የጉምዝ ፤ የሽናሻ ፤ የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች  የአንድነትን እና አብሮ የመኖር ባህልን  የተላበሰ ማህበረሰብ ነው ያለ ሲሆን ፤ ሰሞኑን በተከሰተው ሰብአዊ ቀውስና የሰው ህይወት ህልፈት  ሸንጎው የተሰማውን  ጥልቅ ሀዘን ገልፃôል፡፡

በመተከል ዞን   ግጭት   እንዲፈጠር ያደረጉ ሃይሎች ድብቅ አለማቸውን በህዝብ  ደም ለማሳካት የሚሞክሩ ፅንፈኛ ሃይሎች  የፈጠሩት  እንደሆነ  በመግለፅ፤ ሸንጎው እነዚህ ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ  አሳስቧል፡፡

የመከላከያ ወደ አካባቢው መግባትን የገለፀው ብሔራዊ ሸንጎው ፤ የመከላከያ ወደ አካባቢው መግባት ችግሩን ለመፍታት  መልካም ቢሆንም ለችግሩ  ፀጥታ መረጋገጥና  ዋንኛ መፍተሄ ለማምጣት  ከመተከል  ህዝብ  የሚቀድም የለም ብሏል  ፡፡

በመሆኑም ከሁለቱም ክልሎች እና ከተሞች የሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ  ችግሩ ወደ ተከሰተባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች በመላክ ከፀጥታ አካለት ጋር በመተባበር  ባህላዊ የእርቅ አና  የግጭት አፈታት  ስርዓትን በመከተል ችግሮችን የመፍታት ስራ እንዲሰሩ ሸንጎው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቢንሻንጉል ጉሙዝ  ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት የዜጎቹን ሰባዊና  ዲሞክራሲያዊ መብቶች  ለማሰጠበቅ  የተማôላ  ህገ መንግስታዊ ስልጣን  ያለው በመሆኑ  ትንኮሳን  አደብ ሊያስገዛ እንደሚገባ ሸንጎው አሳስቧል፡፡

በመጨረሻም በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከቤት ንበረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቸን ወደነበሩበት ለመመለስ  ከሚመከለከታቸው  አካለት ጋር በጋራ እየሰራ እንሚገኝም ነው ሸንጎው በመግለጫው የጠቆመዉ፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button