EthiopiaPolitics

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቋል

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቋል

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በድርጅታዊ እና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዩች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔዎችን አሳልፏል ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል ተብሏል፡፡

የሃገሪቱ ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይት በኢኮኖሚው ዘርፍ ማሻሻይዎች ላይ የቀረቡ ሰኖዶችን ገምግሟል ነው የተባለው፡፡

በሃገሪቱ ባለፉት 12 ወራት የተደረጉ የኢኮኖሚ በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ የተወያየው ኮሚቴው ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት መቀዛቀስዝ ስለመከሰቱ ገልጿል፡፡

የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የውጭ እና የውስጥ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባት፣ የስራ ዕድል አለመፈጠር፣ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፉ ላይ የታዩ ክፍተቶች ለኢኮኖሚው መቀዛቀዝ እንደ ምክንያት ተነስቷል ሲል የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት በገፁ አስፍሯል፡፡

በመሆኑም የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ሚና በመወሰን ቀጣይ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ የሚያደርጉ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል ተብሏል፡፡

 

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button