EthiopiaPoliticsSocial

የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተ መንግስት የመጡት አገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተ መንግስት የመጡት አገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍ ታስቦ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤት ቆይታቸው ተናግረዋል።

ሁሉም ወታደሮች ይህን እሳቤ ይዘው ነው የመጡት ለማለት ያስቸግራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊቱ በአንዳንድ ተንኮለኞች የተጠነሰሰ ሴራ እንደነበርም አጋልጠዋል።

በዕለቱ የተወሰደው እርምጃ በጥንቃቄ ባይሆን ኖሮ አገርን ወደቀውስ የሚከት ክስተት ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ወታደሩ ራሱ በሴራው ውስጥ የነበሩትን የድርጊቱን መሪዎች አሳልፎ እየሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ የወታደሮቹን አመጣጥ ወታደራዊ ጥበብ በሚጠይቅ መልኩ አረጋግቶ መመለስ መቻሉ አገርን የማትረፍ ወሳኝ እርምጃ አድርጌ እወስደዋለሁ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button