EthiopiaPolitics

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኔዘርላንድስ ንግስት ማክስሲማንን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኔዘርላንድስ ንግስት ማክስሲማንን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
ንግስቷ አካታች የሆነ የፋይናንስ ስርዐት እንዲጎለብት ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና ያቀረቡት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ፤ አካታች የፋይናንስ ስርዐትን እውን ማድረግ የሚኖረው ፋይዳ በሌሎችም ዘርፎች ላይ በጉልህ የሚንጸባረቅ ነው ብለዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ የአካታች ፋይናንስ ልማት አምባሳደርነታቸው በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ንግስት ማክስሲማን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዘርፉን ለማጎልበት የምታከናውናቸውን ተግባራት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር መወያየታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

አሁንም ግን ውጤታማ የሆነ አካታች የፋይናንስ ስርዓት ለመዘርጋት የሚደረገው ጥረት በተለይም ሴቶችን ያቀፈ ማድረግ እንደሚገባና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት በለየ መንገድ መሰራት እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button