EthiopiaPolitics

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኩባ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር አንቶኒ ጋር ተወያዩ::

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኩባ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር አንቶኒ ጋር ተወያዩ::

አቶ ገዱ እና ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያና በኩባ መካከል ያለውን ዘመናት ያሰቆጠረ ግንኙነት አጠናክረው ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩም መሪዎቹ ተናግረዋል

በሁለቱ አገሮች መካከል በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ ዘርፍ ለዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በተሻለ ለማስቀጠል ይሰራልም ብለዋል አቶ ገዱ ። በተጨማሪም ሁለቱ አገሮች በቀጣይ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ም ተናግረዋል።

የኩባው ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ በበኩላቸው ሁለቱ አገሮች በሁለትዮሽና በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸው ትብብር ውጤታማ ነው ብለዋል። በቀጣይም ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር አጠናክራ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button