EthiopiaPoliticsRegionsSocial

በጂግጂጋ እና ሌሎች ከተሞች የሃገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው የማረጋጋት ስራ መቀጠሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጂግጂጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች በመግባት የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ችግሩን በአንድ ጊዜ ለመመለስ ከባድ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊት በከተሞች በመግባት ችግር ሲፈጠር መቆጣጠርና ማረጋጋት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉንም ነው የተናገሩት።
በስፍራው የተፈጠረውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለማረጋጋት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም የሃገር ሽማግሌዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም መላው ህብረተሰብ አካባቢውን ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት የራሱን ድርሻ እንዲወጣም ጠይቀዋል።
አካባቢውም በመከላከያ ቁጥጥር ስር በመሆኑ ዳግም የሚነሳ ግጭት ስለማይኖር ህብረተሰቡ እንዲረጋጋም ነው የጠየቁት።
በክልሉ ከባድ ጦርነት ሊከሰት ይችላል በሚል የሚነሳው ስጋት አግባብ ባለመሆኑም ነዋሪው ባለበት ተረጋግቶ እንዲጠብቅም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ኤፍ ቢ ሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button