AfricaPolitics

የአፍሪካ ህብረት ሱዳንን ለጊዜው ከአባልነት እንቅስቃሴዋ አገደ፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሱዳንን ለጊዜው ከአባልነት እንቅስቃሴዋ አገደ፡፡

ህብረቱ በአስቸኳይ ስብሰባው በሱዳን የተጀመረው ድርድር በሰላም እስኪጠናቀቅ ሱዳን በአባልነቷ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡

ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው በሱዳን በሲቪሎች የሚመራ መንግስት ካልተመሰረተ ከህብረቱ አባልነቷ ታግዳ ትቆያለች፡፡

የአፍሪካ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት በሱዳን በሲቪል የሚመራ  መንግስት እንዲቋቋም በወታደራዊ ምክር ቤቱ እና በተቃዋሚዎች መካከል የተጀመረው ውይይት በፍጥነት እንዲጀመር አሳስቧል፡፡

በመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ለሳምንታት ተቃውሟቸውን እያሰሙ የከረሙ ሰዎችን ለመበተን በተደረገ ሙከራ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button