World News

ሞሳድ የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል አሲሯል-የኢራን የስለላ ምንጮች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 እስራኤል የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል ማቀዷን ደርሸበታለሁ ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ፡፡ ቴልአቪቭ ይህን የምታርገው በኢራን መረጋጋት እንዳይፈጠር ለማድረግ መሆኑንም አብዮታዊ ዘቡ አብራርቷል፡፡ ተቋሙ በይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ባሰፈረው ጽሁፍ የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቴህራን ውጭ በሚገኙበት ወቅት ግድያው እንዲፈጸምባቸው እቅድ መንደፉን የደህንነት መረጃ ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል ብሏል፡፡


በዚህም የተነሳ ራይሲ የታቀዱ የውጭ ሀገራት ጉብኝቶችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን እንዲሰርዙ የኢራን የደህንነት ተቋም ጉዳዩን ለፕሬዚዳንቱ ቢሮ እንዲያሳውቅ ግዴታ ውስጥ መግባቱን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡ ይህ የሞሳድ ሴራ የተጠነሰሰው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ኢራን ኒውክሌር የማበልጸግ መርሃ ግብሯን የምትቀጥል ከሆነ አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን የሚል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡


ኢራን በበኩሏ ከፍተኛ ጄኔራሏ ከተገደሉባት ወዲህ በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ እንደማትመለስ ደጋግማ ስትገልጽ ትደመጣለች፡፡ ይህን ተከትሎም የእስራኤል ባለስልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዜጎቻቸው ወደ ተለያዩ ሀገራት ሲጓዙ የኢራን ኢላማ እንዳይሆኑ የጥንቃቄ ገለጻ ማድረግ ጀምረዋል ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button