SportSports

8ኛው የሴቶች ዓለም ዋንጫ ውድድር ዛሬ ምሽት ይጀመራል፡፡

በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል/ፊፋ ስር የሚተዳደረው እና ከዛሬ 28 ዓመት በፊት በ1991 ዓ/ም የተጀመረው የፊፋ ሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር በየዓራት ዓመቱ እየተከናወነ ቆይቶ፤ ዛሬ 8ኛው ውድድር በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ይጀመራል፡፡

በ24 ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ይሄ ውድድር ዛሬ ምሽት ሲጀመር በመክፈቻው ጨዋታ ምድብ አንድ ላይ የውድድሩ አዘጋጅ ፈረንሳይ እና ደቡብ ኮሪያ ይገናኛሉ፡፡ ጨዋታው ምሽት 4፡00 ላይ በፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም ይጀመራል፡፡

በውድድሩ ከስድስት ኮንፌዴሬሽኖች የተወጣጡ 24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል ዘጠኝ ከተሞች ላይ በሚገኙ ዘጠኝ ስታዲየሞች ላይ የሚፎካከሩ ይሆናል፡፡

አፍሪካ በሶስት ብሔራዊ ቡድኖች ስትካፈል ካሜሮን፣ ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ይሄንን ዋንጫ ወደ አህጉሩ ለማምጣት ይተጋሉ፡፡

በውድደሩ ከምድብ አንድ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኖርዌይ እና ናይጀሪያ ይገኛሉ፤ ከምድብ ሁለት ጀርመን፣ ቻይና፣ ስፔን እና ደቡብ አፍሪካ ይፎካከራሉ፤

ከምድብ ሶስት አውስትራሊያ፣ ጣሊያን፣ ብራዚል እና ጃማይካ አሉበት፡፡

ከምድብ አራት እንግሊዝ፣ ስኮትላንድ፣ አርጀንቲና እና ጃፓን ይገኛሉ፡፡

ከምድብ አምስት ካናዳ፣ ካሜሮን፣ ኒው ዚላንድ እና ኔዘርላንድስ ተመድበዋል፡፡

ከመጨሻው ምድብ ስድስት ደግሞ አሜሪካ፣ ታይላንድ፣ ቺሊ እና ስዊድን ከምድብ ወደ ሩብ ፍፃሜው ለመሻገር ይፎካከራሉ፡፡

እስካሁን በተካሄዱ ሰባት ውድድሮች አሜሪካ ሶስት ጊዜ ዋንጫ ስታነሳ፣ ጀርመን ሁለት ጊዜ እንዲሁም ካናዳ እንዲሁም ጃፓን እና ኖርዌይ አንድ ጊዜ ባለድል ሆነዋል፡፡

በ8ኛው የሴቶች ዓለም ዋንጫ 27 ዋና ዳኞች እና 48 ረዳት ዳኞች ይመራል፡፡ ከካፍ በኩል 3 ዋና እና 4 ረዳት አርቢትሮች ተመርጠዋል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ደግሞ አፍሪካን ከወከሉ አርቢትሮች አንዷ ነች፡፡

በቪዲዮ የተጋዘ ዳኝነት /ቫር ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ውድድር ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጧል፡፡

ለአንድ ወር የሚዘልቀውን ይሄንን የዓለም ዋንጫ ውድድር ለመታደም አንድ ሚሊዬን ተመልካቾች ቲኬቶችን እንደቆረጡ በቢቢሲ ተጠቅሷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button