EthiopiaSocial

82ኛ ዓመት የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን የመታሰቢያ በዓል በዛሬው ዕለት እየታሰበ ነዉ።

82ኛ ዓመት የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን የመታሰቢያ በዓል በዛሬው ዕለት እየታሰበ ነዉ።

መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ታስቧል

በመታሰቢያ ስነስረዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሌሎች ድርጅቶች ተወካዮች የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርአት አካሂደዋል።

የመታሰቢያ በዓሉ በጣልያን ወረራ ጊዜ በጀነራል ግራዝያኒ ትእዛዝ በሶስት ቀናት ብቻ የተጨፈጨፉ 30 ሺህ ዜጎች የሚታሰቡበት ነው።

በ1929 ዓ.ም የኒፕልስ ልእልት  በመወለዷ ምክንያት ግራዚያኒ ለደስታ መግለጫ ገንዘብ አሰጣለሁ  ብሎ ድሆች በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግስት  በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንደሰበሰቡ አደረገ፡፡

ለእያንዳንዱ ድሃም ሁለት የማርትሬዛ ብር እንዲሰጥም ግራዚያኒ ወስኖ ነበር

ከድሆች በተጨማሪም ታላላቅ የኢጣሊያ ሹማምንቶች፣የሜትሮፖሊቲያኑ ጳጳስና ሌሎች መኳንንቶችም በቦታዉ ነበሩ፡፡

በዚህ ቅጽበት ታዲያ ጀኔራል ግራዚያኒን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ለፋሽስቱ ያደሩ ባንዳዎችና መኳንቶች፣ የፋሽስቱ ባለስልጣናትና ወታደሮች በተገኙበት አስደንጋጭ የሚባለው አደጋ ተከሰተ።

ለፋሽስቱ መገዛት ያንገፈገፋቸዉ  አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ኢትዮጵያውያን የያዙትን የዕጅ ቦንብ ወደ ግራዚያኒ ወረወሩ፥ እናም በዚህ አደጋ እራሱ ጀኔራል ግራዚያኒ ጀርባዉ ቆሰለ  ሌሎች የፋሽስቱ ባለስልጣናትም የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው። በተደገጋሚም 7 ቦንቦች ተጣሉ፡፡

ይህን አደጋ ለመበቀልም በዚያው ዕለት በግቢው ውስጥ የነበሩት  ኢትዮጵያውያን ህይወት ተቀጠፈ።

ቀጥሎም 30 ሺህ የሚሆኑ የተማሩ ወጣቶችን፣ የጦር መኮንኖችና የኃይማኖት አባቶችን፣ እየለቀሙ ያለርህራሄ በጅምላ ጨፈጨፉ፡፡

ይህ ቀን የዛሬ  82 ዓመት የካቲት 12, 1929 ዓ.ም ነበር

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button