COVID-19Health

ቤጂንግ ሮምን አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እያለቻት ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 ቤጂንግ ሮምን አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እያለቻት ነው

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂምፒንግ ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ጣሊያን ቫይረሱን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት በሚገባ እንደግፋለን ብለዋል፡፡

ጣሊያን እና ቻይና ተመሳሳይ ፈተና ገጥሟቸዋል ያሉት ፕሬዝዳንት ሺ፣ ቻይና ቫይረሹን በመከላከሉ ረገድ ተሳክቶላታል ወረርሽኙን ለማጥፋት ከሌሎቹ ሀገራት ጋር ተባበረን  እንሰራለን ብለዋል፡፡

ቫይረሱን የመቆጣጠሯን ነገር እርግጠኛ እየሆነች መምጣቷን ተከትሉ ለዚህ በሽታ መታከሚያ እና ማቆያ እንዲሆኑ የገነባቻቸውን ሆስፒታሎች እየዘጋች ነው፡፡

ሲ ጂ ቲ ኤን እደዘገበው ቻይና ለጣሊያን 9 የጤና ባለሞያዎችን እና 31 ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን ልካለች፡፡

የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በበኩላቸው በዚህ ከባድ ጊዜ የቤጂንግ እና የሮም  የእርደስ በርስ ግንኙነት ይበልጥ ይጠናከራል ነው ያሉት፡፡

ቻይና የቫይረሱ መነሻ በሆነችው የሁቤ ግዛት የበሽታውን ቁጥር በከፍተኛ መጠን የቀነሰች ሲሆን በማቆያ ስፍራ የነበሩ ነዋሪዎችም እንድንቀሳቀሱ በቅርቡ ፈቅዳለች፡፡

ጣሊያን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱባት ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 158 መድረሱን ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button