COVID-19EthiopiaHealthNewsዜና

በደቡብ ክልል ከ12ሺ በላይ ለሆኑ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው ከማረሚያ መውጣታቸውን የደቡብ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

በደቡብ ክልል ከ12ሺ በላይ ለሆኑ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው ከማረሚያ መውጣታቸውን የደቡብ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 የክልሉ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ሙሉሰው ዘውዴን  ጠቅሶ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው  መግለጫ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በመደበኛና በልዩ ሁኔታ ከተለያዩ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች 12 ሺህ 553 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።ጠቅላይ አቃቤ ህጉ እንዳሉት በመደበኛ መንገድ የይቅርታ ተጠቃሚዎችን መረጣና ምልመላ መስፈርት መሰረት ባደረገ መልኩ በአግባቡ የታረሙ፣የታነጹና መልካም ስነ ምግባር ያሳዩ 3 ሺህ 519 ወንድና 119 ሴት እንዲሁም 4 የእስራት ቅነሳ የተደረገላቸው በድምሩ 3 ሺህ 642 ታራሚዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

አቶ ሙሉሰው የክልሉ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ 8 ሺህ 601 ወንድና 310 ሴት በድምሩ 8 ሺህ 911 ታራሚዎች እንዲፈቱ አድርጓል ነው ያሉት።በተለይም ደግሞ ነፍሰ ጡሮች፣ህጻናት ያላቸው፣ልዩ ልዩ ህመም ያለባቸው፣እድሜያቸው የገፋ፣ከ18 አመት በታች የሆኑና አመክሯቸው የተቃረበ ግለሰቦች እንዲወጡ መደረጉን አቶ ሙሉሰው ጠቁመዋል ።እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ሙሉሰው ከህብረተሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜም መልካም አርኣያ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button