COVID-19HealthNews

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያጋራ መኖራያቤቶች የፀረ ተህዋስ  ርጭት ተደረገ ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያጋራ መኖራያቤቶች የፀረ ተህዋስ  ርጭት ተደረገ ::በብርጭቆ ኮንዶሚኒያም ነዋሪ የሆኑት  ኢንጀነር  ሙኩሪያ በየነ  የተባሉ ግለሰብ  በተለምዶ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖርያቤቶች ሳይት የፀረ ተህዋስ ርጭት አካሄደዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን የሚችለውን ጥረት ማድረግ እንዳለበት የገለፁት  ኢንጀነር መኩሪያ በራሳቸው ወጪ 10ሺ ነዋሪዎች የሚኖሩበትን ያጋራ መኖርያቤቶች  የእግረኛ መመላለሻዋች ፤ የመኪና ማቆሚያዎችና መወጣጫዎች ላይ የፀረ ተህዋስ  ርጭት አድርገዎል፡፡

የፀረ ተህዋስ  ርጭት ስራውን ለመስራት  18 ሺ ሊትር  ውሃ እና  270 ሊትር ኬሚካል  የተጠቀሙ ሲሆን የፀረ ተህዋስ  አቀማመም ሂደቱን በተመለከተ  ከድንገተኛ  እሳትና አደጋ ኤጀንሲ  ጋር በመነጋገር መዘጋጀቱን   በመግለፅ ለዚህ ስራ የሚሆን ዘጠኝ ሺ 6 መቶ ብር  ወጪ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ በተለይም ከጤና ሚኒስቴር እና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚተላለፉ መረጃዎችን በመተግበር እንዲሁም ደግሞ ከመንግስት ጎን በመሆን ለችግሩ መረባረብ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button