COVID-19EthiopiaHealthNews

የፌዴራል የትራንስፖርት ባለስልጣን የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2012 የፌዴራል የትራንስፖርት ባለስልጣን የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ገለፀ፡፡
ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸዉ በስድስቱም መናሀሪያዎች ከሚያዚያ 8 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ከዚህ በፊት በሀገራችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት ሲባል ተቋርጦ የነበረዉ የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታዉቋል፡፡የሀገር አቋራጭ ፤ የአነስተኛና መለስተኛ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ትራንስፖርተሮች ተሸከርካሪዎቻችው አገልግሎት ለሚሰጡት ህብረተሰብ አስፈላጊዉን የንጽህና ደረጃ በጠበቀና የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በሚያስችል መልኩ አገልግሎት መስጠት አለባቸው ተብሏል፡፡ለማህበራት ሰራተኞች፣ለአሽከርካሪዎች ፣ ለገንዘብ ተቀባዮችና ለረዳቶች፤ ጓንት፤ የአፍና የአፍንጫ ማስክ፤ ሳኒታይዘር አልኮል የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸውከሚኒስቴር መስርያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የጫኝና አዉራጅ ማህበራት እና የስነስርዓት አስከባሪ አደረጃጀቶችም ለጫኝና አውራጅ እና ለስነ-ሥርዓት አስከባሪዎች ጓንት፤ የአፍና አፍንጫ ማስክ በማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ተሸከርካሪዎች ሥምሪት ከመውሰዳቸው በፊት ከመናሀሪያዉ አስተዳደር ጋር በመሆን የኬሚካል ርጭት በማካሄድ፤ በጉዞ ሂደትም ማንኛዉንም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተሸከርካሪዎቻቸዉ ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ግንዛቤ የሚሰጡ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button