Ethiopia

በግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች የምዝገባ እና የትምህርት ክፍያ ላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ እንደማይደረግ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 27፣ 2012  በግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች የምዝገባ እና የትምህርት ክፍያ ላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ እንደማይደረግ ተገለፀ:: የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከነሃሴ 20 ጀምሮ እንዲከናወን ሚኒስቴር ማስታወቁን ተከትሎ ከተማሪዎች ምዝገባ እና ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ወላጆች ቅሬታን እያቀረቡ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የግል ትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍያ መመሪያን ተላልፈው ምዝገባ እያከናወኑ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጆች ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡ የ2013 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ላይ ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል እና እንደሚያስጠይቅም ገልጿል፡፡ ትምህርት ቤቶችም ምዝገባ ሲያከናውኑ ከዚህ በፊት ይጠቀሙበት የነበረውን የክፍያ አቀባበል ዘዴ መቀየር የማይችሉ መሆኑን እና ከዚህ በፊት በነበረው የክፍያ ስርዓት መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስቧል።

ከዚህም በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ የትምህርት ክፍያ እና ከመመዝገቢያ ክፍያ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ ክፍያ ማስከፈል ማይቻል መሆኑም አሳውቋል፡፡ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ የቀጣይ አመት ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን በተመለከተም ትምህርት ሚኒስቴር እስከሚያሳውቅ ድረስ ማንኛውም ትምህርት ቤት ትምህርት መጀመር አይችልም ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button