COVID-19EthiopiaFeaturedHealthNewsኢትዮጵያ

ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና “ የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና “ የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ::በኮቪድ19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግስት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አቅርቧል።“ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር  ነዉ ውይይት ያካሄደዉ፡፡

ኢትዮጵያ በህገ መንግስቱ መሰረት እስከ ነሃሴ ወር ማለቂያ ድረስ አጠቃላይ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ቢኖርባትም የኮቪድ19 ወረርሽኝ ምርጫን ማከናወን የማያስችል ደረጃ ላይ በማድረሱ ምክንያት ህግና እውነታውን አጣጥሞ መሄድ አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምክትል አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንዳሉት ችግሩን ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማያፋልስ መልኩ ለመቅረፍ አራት የመፍትሄ አማራጮች ተቀምጠዋልብለዋልየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፤ ህገ መንግስትን ማሻሻል እና የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button