EducationEducationEthiopiaFeaturedHealthRegions

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ለሦስት ምሁራን የፕሮፌስርነት ማዕረግ ሰጠ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በማስተማርና ምርምር ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታዉቋል። የዩኒቨርስቲው ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እምሩ ለኢዜአ እንደተናገሩት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠው በተሰማሩባቸው የማስተማርና የምርምር መስኮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምሁራን ነው።

የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ የተሰጠውም ለዶክተር ይሄነው ገብረስላሴ በአፈር ሳይንስ ፣ ለዶክተር አብርሃ ፀጋዬ በፕላንት ኢኮሎጂ ኤንድ ኢትዮ ቦታኒ እንዲሁም ለዶክተር ከፍያለው አለማየሁ በእንስሳት ብዜት የትምህርት ዘርፎች የላቀ ውጤት በማስመዘገባቸው እንደሆነ አብራርተዋል። ምሁራኑ በዩኒቨርስቲው በመማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን በማካሄድና ፅሁፎቻቸውን በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት በሚገኙ ጆርናሎች በማሳተም እውቅና ያተረፉ በመሆናቸው ነው ብለዋል ። ሙሁራኑ በተጨማሪም ተማሪዎችን በማማከር፣ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ተመድበው በሰጡት የአመራር ብቃትና ባስመዘገቡት ውጤት ተመዝነው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድተዋል ።የምሁራኑን አስተዋጽኦ የዩኒቨርስቲው ሴኔት ገምግሞ ያቀረበውን ውጤት በስራ አመራር ቦርድ በማፀደቅ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው ከዶክተር ዘውዱ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button