Ethiopia

በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። ሰሞኑን የታየው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የመጣ መሆኑ
ተጠቁሟል።


በኢንስቲትዩቱ የአየር ሁኔታና የአየር ጠባይ ትንበያ ባለሙያው ታምሩ ከበደ እንደገለጹት፤በቀጣዩ ክረምት ወቅት ከመደበኛው በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ትንበያዎች ያመለክታሉ። የላሊና የአየር ጠባይ ለውጥ ሳቢያ በአሀገሪቱ በበልግም ሆነ በመኸር ወቅቶች ደረቅ ወራት በዝተው መስተዋላቸውን የገለጹት ባለሙያው ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሀምሌና ነሀሴ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል ብለዋል።

በተለይም በሀገሪቱ በሰሜን ምስራቅና በምስራቅ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ እየጨመረ እንደሚሄድ ጠቁመዋል። ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው ከፍተኛ የሙቀት መጠን የላሊኖ ተፅእኖ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጋር ተያያዥ መሆኑን ለጎርፍ አደጋ ሥጋት እንደሚሆንም አብራርተዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ከወዲሁ አደጋዎች እንዳይፈጠር ኅብረተሰቡም ሆነ ተቋማት ከወዲሁ የመከላከል ሥራ ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።


በተለይ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ፣በወንዞችና ተዳፋታማ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጠናከረ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በሀገሪቱ የተከሰተው ላሊና የመኸርና በልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑትን የቦረና፣ባሌ ሶማሌና ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች በቂ ዝናብ እንዳያገኙ ምክንያት መሆኑንም አስታውሰዋል።


የአደጋ ሥጋትና አመራር፣ ጤና ሚኒስቴር፣ ግብርናና ሌሎች መሰል የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላሊኖ የሚፈጥረውን አደጋ ለመመከት ከወዲሁ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ከግንቦት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የሙቀቱ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በከተሞች መስፋፋትና የውኃ አካላት መመናመን ምክንያት መሆኑንም ነው ያነሱት። ኅብረተሰቡም የተለያዩ ተክሎችን በመትከልና በመንከባከብ የአየር ንብረት ለውጥን የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች መቋቋም እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button