crimeNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ የሀገራቸውን የፍትህ ስርዓት አጣጣሉ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ የሀገራቸውን የፍትህ ስርዓት አጣጣሉ::በሳምንቱ መጨረሻ ቀን በኢየሩሳሌም አውራጃ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው የክስ ሂደታቸውን የተከታተሉት ኔታኒያሁ የተከሰስኩት በሀሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡የክሱ ዋና ዓላማ ጠንካራውን ጠቅላይ ሚስትር ከስልጣን ለማውረድ ቢሆንም ይህ ግን አይሳካም በማለት ሀገራቸውን በታማኝነት መምራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ኔታኒያሁ እሳቸው የሚመሩትን የቀኝ ዘመም ፖለቲካ አራማጅ የሆነውን ሊኩድ ፓርቲ የአመራርነት ቦታ እንዳይኖረው የተሸረበ ሴራ ነው ብለውታል ክሱን፡፡አልጀዚራ እንደዘገበው ኔታኒያሁ ፍርድ ቤት ቀርበው ስለክሳቸው በሰጡት መልስ ዳኞች፣አቃቤ ህጎች፣ ፖሊስ እና ሚዲያው ተባብረው አንዳች ተንኮል እንደሰሩባቸው ተናግረዋል፡፡በጉቦ ቅሌት፣ በእምነት ማጉደል እና በማጭበርበር በሶስት ወንጀሎች ክስ የተመሰረተባቸው ኔታያሁ እስራኤልን ለረጅም ጊዜ በመምራት እና በስልጣን ላይ እያሉ የተከሰሱ ብቸኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button