COVID-19

ሰሜን ኮሪያ ትምህርት ቤቶችን በድጋሚ ልትከፍት ነው፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 ሰሜን ኮሪያ ትምህርት ቤቶችን በድጋሚ ልትከፍት ነው፡፡
ሰሜን ኮሪያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመለከላከል ዝግ አድርጋ የቆየቻቸውን ትምህርት ቤቶችን በያዝነው የፈረንጆቹ ወር ልትከፍት መሆኑን አስታውቃለች፡፡
ፒዮንግያንግ እስከአሁን አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሪፖርት ያላደረገች ቢሆንም ድንበሮቿን መዝጋትን ጨምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን በለይቶ ማቆያ እስከ መለየት የሚደርስ ጠናካራ ህጎችን ተግባራዊ አድርጋለች፡፡
የሀገሪቱ መንግስት በፈረንጆቹ ሰኔ ወር የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ይጀመራል ብሏል፡፡
የትምህርት ባለስልጣናት ትምህርት ይጀመር ከተባለ ለመምህራንና ለተማሪዎች የሙቀት መለኪያ መሳሪያና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ሊሟላላቸው ይገባል በማለት ጠይቀዋል፡፡ሀገሪቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን አስመልክቶ የምታወጣው ሪፖርት በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በከፍተኛ ጥርጣሬ ይታያል ሲል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button