COVID-19EthiopiaNews

የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ጋር በሰፊው የሚዋሰን በመሆኑ በድንበር የሚገቡ ዜጎችን ለመቆጣጠር ፈታኝ ሆንዋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ጋር በሰፊው የሚዋሰን በመሆኑ በድንበር የሚገቡ ዜጎችን ለመቆጣጠር ፈታኝ ሆንዋል ተባለ፡፡
የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ፤ ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሰፊው እንደሚዋሰን የጠቆሙት አቶ ኡሞድ በድንበር አካባቢ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት እየተሰራ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የመግቢያና የመውጫ በሮች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝግ ቢደረጉም በህገ ወጥ መንገድ የሚገቡ ዜጎችን የአካባቢ ሚኒሻዎችን በመጠቀም ማስቆም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የኑዌር ብሄረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙድ ቶክ በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ መከሰቱ ከታወቀ ጀምሮ በዞኑ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ስርጭቱን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡ በዞኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በርካታ ተግባራት ቢከናወኑም ዞኑ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሰፊው የሚዋሰን በመሆኑ በድንበር አካባቢ የሚገቡ ዜጎችን ለመቆጣጠር ፈታኝ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የ12ኛ ክፍለ ጦር የ3ኛ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ አዛዥ ሻምበል ኤፍሬም የትሻወርቅ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለም ሀገራትን ጭምር እየፈተነ ያለ ወረርሽኝ በመሆኑ በሀገራችንም ቫይረሱን ለመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል፡፡በዚህም በድንበር አካባቢ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር በቅንጅት እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button