EconomyEthiopia

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ስምምምነትን ለአፍሪካ ህብረት አቀረበች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ስምምምነትን ለአፍሪካ ህብረት አቀረበች
ኢትዮጵያ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል ያጸደቀችውን የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት  ለአፍራካ ህብረት ገቢ አድርጋለች።

በፕሮግራሙ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ ተገኝተዋል።

የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በዚሁ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የኢንዱስትሪ እና የተቋማትን ተወዳዳሪነት በማሳደግ በአህጉሩ ያሉ የገበያ እድሎችን አሟጦ ለመጠቀምና ሃብቶችን በአስፈላጊ አካባቢዎች እንዲገኙ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

የ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው ውሳኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠንካራ ቀጣናዊ ትስስር እንዲኖርና ነጻ የሰዎችና የሃሰብ ዝውውር እንዲስፋፋ ካላቸው ራዕይ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ስምምነት በአፍሪካውያን መካከል ያለውን ንግድ እንደሚያሳድገው፤ በቀጣናዊ የንግድ ማህበረሰቦች መካከል ብሎም በአህጉር ደረጃ የበለጠ ትስስር እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

ስምምነቱ ከዓለም የንግድ ድርጅት ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በአፍሪካ ትልቁ የንግድ ስምምነት ይሆናል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ነው

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button