EthiopiaRegions

የጋሞ ዞን ምክር ቤት አባላት የማህበረሰቡ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ፍላጎት አለን አሉ

የጋሞ ዞን ምክር ቤት አባላት የማህበረሰቡ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ፍላጎት አለን አሉ

አርትስ 05/04/2011

 የምክር ቤቱ አባላት የማህበረሰቡ መለያ የሆነውን የግጭት አፈታት ባህል በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ምዝገባው እንዲከናወን ፍላጎት አለን ብለዋል።

ባህሉ ለልማት፣ለሰላም፣ለመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፋይዳ አለው ያሉት አባላቱ ይህም ለሌላው አለም ጭምር መማሪያ ነው ብለዋል።

ባህሉ ሴቶች ነጠላቸውን በማንጠፍ ሰላም እንዲወርድ የሚያደርጉበት ስርዓት ሲሆን  ከአጼዎቹ ሥርዓት ጀምሮ በዳራማሎ፣በቦንኬ፣ በጨንቻና በሌሎች የዞኑ አካባቢዎች ግጭቶች ሲከሰቱ  ባህላዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ሲካሄድ ቆይቷል።

ባህሉን ተላልፎ ጥፋት መፈጸም በማህበረሰቡ ዘንድ ”ጎሜ” ወይም የሚያስቀስፍ ነው ተብሎ ስለሚታመንና ጥፋት ፈጻሚው በሕዝቡ እንዲገለል ያደርጋል። ስለሆነም ግጭቱ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ ለመፍታት ያስችላል።

ባህሉ ግጭት ሲከሰት ሳር ይዘው የሚያስቆሙ አባቶች ብቻ ሳይሆን እናቶችም ነጠላቸውን መሬት ላይ በማንጠፍ የሚያወግዙበት ነው።

የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አርኮ ደምሴ ሰላም ለሰው ልጆች ያለውን ጥቅም በመረዳት ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ይህንን ባህላዊ እሴት በድርጅቱ ለማስመዝገብ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።  ዜናው የኢዜአ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button