NewsWorld News

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለፍልስጤማዊው ወጣት ሞት ይቅርታ ጠየቁ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለፍልስጤማዊው ወጣት ሞት ይቅርታ ጠየቁ :: የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታያሁ ለወጣቱ እናት የይቅርታ መልእክታቸውን ያተላለፉት ከተገደለ አንድ ሳምንት ካለፈው በኋላ ነው፡፡ እየሩሳሌም ውስጥ በእስራኤል ፖሊሶች የተገደለው የ32 ዓመቱ ወጣት ኢያድ ሀላክ ከልጅነቱ ጀምሮ የኦቲዝም ታማሚ ነበር ተብሏል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ ራሱን መከላከለ በማይችል ሰው ላይ የተፈፀመውን ግድያ ትራጄዲ ብለውታል፡፡ በመግለጫው ወቅት በቅርቡ ከኔታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲ ጋር የጥምር መንግስት የመሰረቱት የብሉ ኤንድ ዋይት ፓርቲ መሪው ቤኒ ጋንትዝም ተገኝተዋል፡፡ ጋንትዝ በወጣቱ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአደባባይ አውግዘው ዳግም እንዳይደገም ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ይሁን እንጂ ወጣቱን ሀላክን የገደለው ፖሊስ ከእስር ተለቆ በቁም እስር በቤቱ እንዲቀመጥ መደገረጉ
በፍልስጤማዊያን ዘንድ ዳግም ቁጣን ቀስቅሷል ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button