AfricaTourism

በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ጽንፈኛ ጂሃዲስቶች ሳይፈጽሙት አልቀረም በተባለ ጥቃት በትንሹ 59 ሰዎች ተገደሉ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012 በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ጽንፈኛ ጂሃዲስቶች ሳይፈጽሙት አልቀረም በተባለ ጥቃት በትንሹ 59 ሰዎች ተገደሉ።የጂሃዲስት ታጣቂ ቡድን በሰሜናዊ ናይጄሪያ ባደረሰው ጥቃት በትንሹ 59 ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ በቦርኖ ግዛት ስር በምትገኝ ጉቢዮ በምትባል የገጠር መንደር ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ንጹሃን ዜጎችን መግደላቸውን ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያስረዳው፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመባት መንደር ሙሉ ለሙሉ ውድመት የደረሰባት ሲሆን ከአከባቢው የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው በቀጣይ የበቀል እርምጃ ሊፈጸም ይችላል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት የመንደሯ ነዋሪዎች መረጃዎችን ለደህንነት አካላት ነግረውብናል የሚል ነው፡፡ ምንም እንኳ ለዚህ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ጂሃዲስቱ ቦኮ ሃራም በሰሜን ናይጄያ ግዛት ለሚፈጸሙ ተመሳሳይ ጥቃቶች ኃላፊነቱን ሲወስድ ቆይቷል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button