አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 የኬንያ ፖሊሶችስ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ ተኩሰው ሶስት ሰዎች መግደላቸው ተሰማ:: ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት የታክሲ ሾፌሮች እና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ሲሆኑ ምክንያታቸውም የሥራ ባልደረባቸው የሆነ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ህግን ተላልፏል ተብሎ በመታሰሩ ነው ተብሏል፡፡ የኬንያ ፖሊስ ኢስፔክተር ጄኔራል ሂላሪ ሙቲያማቢያ በሰልፎቹ ላይ ተኩሰው የሰው ህይዎት እንዲያልፈ ምክንያት ናቸው የተባሎ የፖሊስ አባላት እንዲታሰሩ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ በፖሊሶቹ እርምጃ የተበሳጩት ሰልፈኞቹ የአንድ የፖሊስ መኮንን ቤት ማቃጠላቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎቹ መካከል ግጭቱ የተፈጠረው ሌሶስ በተባለችው የኬንያ ከተማ ሲሆን ፖሊስ ጥይት ለመተኮስ ያስገደደው ተቃዋሚዎቹ በህግ አስከባሪዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘራቸው መሆኑን ተናግሯል፡፡የኬንያ ፖሊስ በዜጎች ላይ ከልክ በላይ የሆነ ሃይል ይጠቀማል የሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ የሚደርስበት ሲሆን ከአሁን ቀደምም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች ከእንቅስቃሴ እገዳ ጋር በተያያዘ መገደላቸው ተነግሯል፡፡
With Product You Purchase
Subscribe to our mailing list to get the new updates!
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur.
Related Articles
Check Also
Close
-
የኢትዮጵያን ስም የሚያጠለሸው አዋጅ ውድቅ ተደረገ::December 16, 2021