World News

ኢራን በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኝ የእስራኤል ጦር ሰፈር ላይ የድሮን ድብደባ ማደረሷ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 ቴህራን ይህን እርምጃ የወሰደችው ባለፈው ወር የእስራኤል አየር ሃይል በአንድ የድሮን ፋብሪካዋ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ለመበቀል ነው ተብሏል፡፡ እስራኤል ጥቀት ፈጸመችበት የተባለው ፋብሪካ የኢራን ሁነኛ የወታደራዊ ድሮኖች ማምረቻና ማከማቻ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡


ይሁን እንጂ እስራኤል እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ማስተባበያም ይሁን ድርጊቱን ስለመፈፀሟ አንዳችም መግለጫ አልሰጠችም፡፡ ደረሰ የተባለው ጥቃትም ቢሆን እስካሁኑ ሳምንት ድረስ በሚስጥር ተይዞ ቆይቶ አል ማያዲን የተባለ የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው ይፋ ያወጣው ተብሏል፡፡ የገልፍ ሀገራት ለእስራኤል የጦር ሰፈር እድታቋቁም እንዳይፈቅዱ የሚያስጠነቅቅ መልእክት ማስተላለፏን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡ ከአሁን ቀደም ከኒውክሌር ማብለያ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያላቸው ተቋሞቼ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሰንዝራብኛለች በማለት እስራኤልን የምተከሰው ኢራን እሷም ከአጸፋ እርምጃ እንደማትመለስ ተናግራለች፡፡ በተለይ የኒውክሌር ሳይንስ ሊቅ የሆኑት ግለሰብ በእስራኤል ሃይሎች ከተገደሉባት ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መካከል መካረሩ ተባብሶ ቀጥሏል ነው የሚባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button