AfricaNews

አልበሽር ከ30 ዓመታ በፊት ፈፀሙት በተባለ የመፈንቅለ መንግስት ክስ ፍርድ ቤት ቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ15፣ 2012 አልበሽር ከ30 ዓመታ በፊት ፈፀሙት በተባለ የመፈንቅለ መንግስት ክስ ፍርድ ቤት ቀረቡ:: የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1989 በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የጠቅላይ ሚኒስትር ሰዲቅ አል መሃዲን መንግስት በሃይል
ገልብጠዋል ተብለው ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አልበሽር በተከሰሱበት የመፈንቅለ መግስት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የሞት አልያም የእእድሜ ልክ እስር ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡አልበሽር ከአንድ ዓመት በፊት በህዝባዊ አመፅ ከስልጣናቸው ከወረዱ ወዲህ ህገ ወጥ ገንዘብ ተገኝቶባቸዋል በሚል ክስ ሁለት ዓመት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ገና ያልተቋጩ በርካታ ክሶች ያሉባቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት በዚሁ ጉዳይ 10 ወታራዊ ባለስልጣናት እና ስድስት ሲቪል ሰዎችም አብረዋቸው ተከሰዋል ተብሏል፡፡ አልበሽር በስልጣን በነበሩበት ወቅት በእሳቸው ትዕዛዝ ተፈፅሟል በተባለው የዳርፉር የጦር ወንጀል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የሚፈለጉ ሲሆን የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ተላልፈው ይሰጡ በሚለው ጉዳይ ላይ ውሳኔውን በግልፅ አላሳወቀም፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button